አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝ ስዊዘርላንድን በመለያ ምት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች።
በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ምሽት 1 ሰዓት ላይ እንግሊዝ እና ስዊዘርላንድ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
ብሄራዊ ቡድኖቹ በመደበኛ እና በተጨማሪ ሰዓት 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት በማጠናቀቃቸው ወደ መለያ ምት አምርተዋል፡፡
በዚህም እንግሊዝ ስዊዘርላንድን በመለያ ምት 5 ለ 3 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል ችላለች፡፡
የሩብ ፍጻሜው መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 4 ሰዓት ላይ ቱርክ እና ኔዘርላንድስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡