Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

1 ሺህ 148 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 148 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ 1ሺህ 143 ወንዶች እና 5 ሴቶች ሲሆኑ ፥ ከእነዚህም መካከል 128 ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ57 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version