Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሚዲያ ባለሙያዎች በመናበብ ለሀገራዊ ምክክሩ አስተዋጽኦ ማድረግ አለባቸው – መስፍን አርአያ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተናበበ ሥራ በማከናወን ለሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ያዘጋጀው የሥልጠናና የውይይት መድረክ ተጠናቅቋል።

ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት ፥ ጋዜጠኞች በዚህ መሰል የሥልጠናና የውይይት መድረክ መሳተፋቸው በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ የበለጠ ለማጠናከር ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል።

ባለሙያዎቹ የተናበበ የሚዲያ ሥራ በማከናወን ለሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባቸው ነው ያሳሰቡት።

እስካሁን ለነበራቸው ተሳትፎ ምስጋና ያቀረቡት ዋና ኮሚሽነሩ ፥ ጋዜጠኞች በቆይታቸው ላነሷቸው ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በስልጠናና የውይይት መድረኩ የሚድያ ፎረም አመራሮችን ጨምሮ ከ40 በላይ ከሚሆኑ የሀገር ውስጥና የውጪ የሚድያ ተቋማት የመጡ ከ100 በላይ ጋዜጠኞች መሳተፋቸው ተጠቁሟል፡፡

መገናኛ ብዙሃን በሀገራዊ ምክክሩ ያላቸውን አዎንታዊ ሚና የበለጠ ለማጠናከር ያለመ በማኅበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ባለሙያዎች ጋር ነገ ተመሳሳይ ውይይት እንደሚደረግም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version