የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኦርዲን በድሪ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አስጀመሩ

By Shambel Mihret

July 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አስጀመሩ።

መርሐ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

አቶ ኦርዲን በድሪ የአየር ንብረት ለውጥ የአፈር መሸርሸር ከፍተኛ ችግር ሆኖ መቆየቱን አስታውሰው፤ ይሄንን ችግር ለመፍታት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር አበረታች ለውጥ አምጥቷል ብለዋል።

በዘንድሮው መርሐ ግብር በሐረሪ ክልል 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን አንስተው፤ 26ኛውን ዓለም አቀፍ የሐረር ቀንን አስመልክቶ ወደ ሀገራቸው ከመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ ጋር 500 ሺህ ችግኞችን በአንድ ጀምበር ይተከላል ብለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተጀመረው መልካም ስራ የሐረርን ስልጣኔ እና ታሪክ በሚመጥን መልኩ በሁሉም ስራች ሊደገም ይገባል ተብሏል።

በሜሮን ሙሉጌታ