አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አሥተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
የሀገራቱ የጋራ ድንበር አሥተዳዳሪዎች ያካሄዱትን ምክክር አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ-ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አሥተዳዳሪዎች የምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት በስኬት መጠናቀቁን አስታውቀዋል፡፡
ሀገራቱ በልማት ትብብር፣ በድንበር አካባቢ በጋራ ሰላምን ለማስጠበቅ፣ የመሠረተ-ልማት ዝርጋታና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በይበልጥ ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ብትብብር ለመሥራት ከስምምነት መድረሳቸውም ተመላክቷል፡፡
በመራኦል ከድር