Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በብሪታኒያ ጠቅላላ ምርጫ የሌበር ፓርቲ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብሪታኒያ በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ የሌበር ፓርቲ ማሸነፉ ተገለፀ፡፡

ሌበር ፓርቲ እስካሁን ከብሪታኒያ 650 ወንበሮች 411 ያህሉን በማግኘት ነው ጠቅላላ ምርጫውን ማሸነፍ የቻለው፡፡

በውጤቱ መሰረት የሌበር ፓርቲው መሪ ኬር ስታርመር የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ መሪ ሪሺ ሱናክ በመተካት የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናሉ ተብሏል፡፡

ለ14 ዓመታት ያህል ሀገሪቱን ሲያስተዳድር የነበረው ኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ እስካሁን 119 ወንበር ማግኘቱ የተረጋገጠ ሲሆን፤ በምርጫው አስከፊ ሽንፈት ገጥሞታል ነው የተባለው፡፡

ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ምርጫውን ሌበር ፓርቲ ማሸነፉን ያመኑ ሲሆን ፓርቲያቸው ለገጠመው ሽንፈት “ሙሉ ኃላፊነቱን እወስዳለሁ” ብለዋል፡፡

የሌበር ፓርቲ መሪ ኬር ስታርመር በበኩላቸው ለደጋፊዎቻቸው “አሳክተነዋል” ሲሉ ማሸነፋቸውን መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version