የሀገር ውስጥ ዜና

ተረጂነት የሀገርን ክብርን ዝቅ እንደሚያደርግ ግንዛቤ በመገንዘብ ጠንክሮ መስራት ይገባል – አቶ እንዳሻው ጣሰው

By Melaku Gedif

July 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተረጂነት የሀገርን ክብር እና ሉዓላዊነትን ዝቅ እንደሚያደርግ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ከችግር ለመውጣት ጠንክሮ መስራት ይገባል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡

በክልሉ “ጸጋዎቻችንን በማልማት፣ በምግብ እራሳችንን ለመቻል እንተጋለን፤ ተረጂነትን እንቀለብሳለን” በሚል መሪ ሃሳብ የአመራር የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

አቶ እንዳሻው ጣሰው በዚህ ወቅት÷ ከአንድ ወር በፊት ከክልሉ አመራር ጋር ከተረጂነት ወደ ምርታማነት እንዴት መሻገር አለብን በሚል ዝርዝር ውይይት መደረጉን አስታውሰዋል።

በክልሉ የተደረገውን ውይይት በየደረጃው ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ማስጨበጥ መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

ተረጂነት ክብርን እና ሉአላዊነትን ዝቅ እንደሚያደርግ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ወደ ተግባር እንደተገባ ማስረዳታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ተረጂነትን በተግባር እና በአስተሳሰብ ደረጃ መቀልበስ እንደሚገባ ከስምምነት ላይ መድረስ መቻሉን ጠቁመዋል።