Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፋር ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ የክልሉን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአሚባራ ወረዳ ሲደሃ ፋጊ ቀበሌ አስጀምረዋል።

ዛሬ በተጀመረው የክልሉ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በ250 ሄክታር መሬት ላይ ችግኝ ተተክሏል።

የአሚባራ እርሻ ልማት ሰራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በተለይም የብርቱካንና ፓፓዬ ችግኞች በብዛት መተከላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህ ወቅት ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እንዳሉት÷ ህዝባችን ችግኝ የመትከልና የተተከሉት ዛፎች እስኪፀድቁ ድረስ የመንከባከብ ልማድን ማሳደግ ይገባል።

የሚተከሉት ችግኞች ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያላቸው ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በዚህም የህዝቡ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን አንስተዋል።

Exit mobile version