አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግስት ማካሄድ አይሳካም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከም/ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ እየሰጡ ነው፡፡
በዚህ ወቅትም በቅርቡ አንዳንድ ቦታ ላይ መፈንቅለ መንግስት እናካሂዳለን ብለው አንዳንድ አባቶቻችን ውይይታ ያደርጋሉ ሲሉ አንስተዋል፡፡
እናም ለወንደሞቼ እና ታላላቅ አባቶች የምሰጠው ምክር በኢትዮጵያ መፈንቅለ መንግስት አይሳካም የሚል ነው ብለዋል፡፡
እኛ ወታደሮች ነን መፈንቅለ መንግስት እንዳይሳካ አድርገን ነው ተቋማትን የሰራነው ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ከ50 ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግስት አንዴ ተሳክቷል፣ አሁን ግን ጭራሽ አይሳካም ነው ያሉት፡፡
ስለሆነም ታላላቆቼ እና አባቶቼ ጊዜያችሁን እና የወዳጆቻችን ሀገር ገንዘብ አታባክኑ፤ ገስት ሃውስም አታጣቡ ሲሉ መክረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ላይ በግጭት፣ በጦርነት፣ በሽፍታነትና በመፈንቅለ መንግስት ሥንጣን መያዝ እንደማይቻልም አስገንዝበዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ