አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደበኛ ስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
እንዲሁም ምክር ቤቱ የ2017 የፌዴራል መንግስት በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አዳምጦ ረቂቅ በጀቱን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
በመደበኛ ስብሰባ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡