Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ግብረ ሃይሉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ሃይል ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ተማሪዎች የለፉበትን የትምህርት ውጤት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለፈተና ቁሳቁሶች እጀባ፣ ጥበቃ እና ፍተሻ እንደሚያደርግ ገልጿል።

ኅብረተሰቡ ይህንን አውቆ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባዘጋጀው የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) በመጠቀም ጥቆማ እንዲሰጥ ግብረ ሃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመደወልና መረጃ በመላክ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በአካል ጥቆማ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረ ሃይሉ ጠይቋል፡፡

Exit mobile version