አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 1 ሺህ 381 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።
ከተመራቂ ተማሪዎቹ መካከልም 273ቱ ሴቶች ሲሆኑ 1 ሺ 108ቱ ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በ2ኛ ዲግሪ መርሐ-ግብር በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ህግ፣ ግብርና፣ ጤና እና ሌሎች የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን÷ ዘንድሮ በልዩ ሁኔታበጤና ስፔሻሊቲ ዘርፍ አምስት የውስጥ ደዌ ስፔሻሊቶችን አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር በሽር አብዱላሂ÷ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ በኩል ዩኒቨርሲቲው ስኬታማ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ መናገራቸውን የሶማሊ ክልል መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ጥናቶችና ምርምሮችን ላይ በስፋት እየሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ በክልሉ ተከስቶ የነበረውን ድርቅ ለመከላከል በተከናወኑ ስራዎች ላይ አስተዋፅዖ ማበርከቱን አስታውሰዋል።