አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ገጣሚ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ነቢይ መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
ገጣሚ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ነቢይ ባደረበት ህመም ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የደራሲው የቅርብ ቤተሰቦች አስታውቀዋል፡፡
ነቢይ መኮንን በህትመት ሚዲያ ዘርፍ ዋና አዘጋጅነትን ጨምሮ በርካታ በነበረው አገልግሎት የተለያዩ ስራዎቹን ለአንባቢያን አድርሷል።
የተለያዩ መጽሕፍትን ከመተርጎም ባለፈ የግጥም ሥራዎችን ለተደራሲያን ሲያቀርብ መቆየቱም ይታወቃል፡፡