አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት የማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አንቶኒ ካፑአኖ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው÷ በማደግ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ የጉዞ እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ላይ መክረዋል።
በባህል ሀብቷ እና ታሪካዊ ቅርስ ይዞታዋ ብሎም በአስደናቂ የመልክዓ ምድር ገፅታዋ የታወቀችው ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዋን በማስፋፋት ላይ አተኩራለች መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዓለም ዙሪያ 8 ሺህ 785 ያህል ቅርንጫፎች እና የሀብት አድራሻዎች በመያዝ በመስተንግዶ እና ማረፊያ አገልግሎት ዘርፍ መሪ የሆነው ማሪዮት ኢንተርናሽናል በዚህ ስራ ጉልህ ሚና ለመጫወት ትልም ይዟል ተብሏል።