Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአቶ አረጋ ከበደ የተመራ ልዑክ ኮምቦልቻ ከተማ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የተመራ ልዑክ ኮምቦልቻ ከተማ ገብቷል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የከተማዋ ከንቲባ መሃመድ አሚን የሱፍን ጨምሮ ሌሎች የዞን የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከአቶ አረጋ በተጨማሪም የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ ፣ የአማራ ክልል ም/ቤት አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

አቶ አረጋ በኮምቦልቻ ቆይታቸው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን እንደሚያስጀምሩ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version