አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተሞች የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ሰለሞን ገለጹ፡፡
ከተሞችን ውበት እያጎናጸፉ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች የስራ ዕድል እየፈጠሩ እንደሚገኙም አመልክተዋል።
የከተማ መሬት አስተዳደርና ፕላን ሲዘጋጅ 30 በመቶ ለመንገድ፣ 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት እንዲሁም 40 በመቶ ደግሞ ለተለያዩ የግንባታ አገልግሎቶች እንዲውል በመደንገግ መሆኑን አንስተው፤ ይህን አዋጅ መነሻ በማድረግ የከተሞች ኮሪደር ልማት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት መነሻ በማድረግ በክልሉ በሚገኙ ከሞች የኮሪደር ልማት መጀመሩንም ተናግረዋል።
ክልሉ ስድስት ከተሞችን ማዕከል በማድረግ የተመሠረተ መሆኑን ያስታወሱት ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን፤ አሁን ላይ በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭ እና ዲላ ከተሞች የኮሪደር ልማቱ በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማቱ በቀጣይ በቀሪ ክላስተር ከተሞች እና በክልሉ በሚገኙ የከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ ለማድረግ ክልሉ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸው÷ ልማቱ ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ