ስፓርት

የ2017 የውድድር ዘመን የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ ይፋ ሆነ

By ዮሐንስ ደርበው

July 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ2017 የውድድር ዘመን የተጫዋቾች የዝውውር ጊዜ ይፋ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡

በዚህም መሠረት ከሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የዝውውር ጊዜው ክፍት ሆኖ ይቆያል መባሉን የፌደሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡