ፋና ስብስብ

በተመሳሳይ ውጤት የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት መንትዮች

By Meseret Awoke

July 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡

ዮሴፍ ሞላወርቅ እና ሰለሞን ሞላወርቅ ይባላሉ፡፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ጅማ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በባዮሜዲካል ምህንድስና ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡

መንትዮቹ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና በጥሩ ውጤት ማጠናቀቅ መቻላቸውም ነው የተሰማው፡፡

መንትዮቹ ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ በአንድ ክፍል የተማሩና በጅማ ዩኒቨርሲቲ በባዮሜዲካል ምህንድስና ቆይታቸውም ተመሳሳይ ውጤት (ሲጂፒኤ) እና የተቀራረበ የመውጫ ፈተና ውጤት በማምጣት ለምረቃ በቅተዋል።

ተመራቂ ዮሴፍ ሞላወርቅ የመውጫ ፈተናውን 71 ነጥብ ያመጣ ሲሆን፥ መንታ ወንድሙ ሰለሞን ሞላወርቅ ደግሞ 73 በማምጣት አጠናቅቀዋል ነው የተባለው።

ሁለቱ መንትዮች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ጥሩ ጊዜ ማሳለፋቸውን ገልፀው፥ ወደፊት በሚሰጣቸው ሀገራዊ ኃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት ሀገራቸውን እንደሚያገለግሉ መግለጻቸውን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡