Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሀገር አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሚዲያዎቻችን ለዘላቂ ሰላማችን “የተሰኘና ለሚዲያ አካላት የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው::

የሰላም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ ኮንፍረንሱ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ የዘርፉ ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ::

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እንድሪስ በዚሁ ወቅት÷ መገናኛ ብዙሃን አብሮነትን የምናሳድግበት እንጂ ላልተፈለገ ድርጊት የምንጠቀምበት ሊሆን አይገባም ብለዋል፡፡

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱአለም በበኩላቸው÷ መገናኛ ብዙሃን የሀሳብ ብዝሀነትን በማሳደግ የህዝብ አይንና ጆሮ በመሆኑ ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ የጎላ ጥቅም እንዳለው ጠቁመዋል።

ይህም ሆኖ ቢሆንም በተለይ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ፈር ካልተበጀለት በሀገር ላይ የሚያደርሰው ጉዳት የከፋ እንደሚሆን አስገንዝበዋል::

በዘረያቆብ ያቆብ

Exit mobile version