Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ልዑክ በኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ሞተራይዝድ ሻለቃን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ልዑክ በኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ሞተራይዝድ ሻለቃን ጎብኝቷል፡፡

በኬኒያ ናይሮቢ ከሚገኘው የምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ቢሮ የተውጣጣ ልዑክ ኢትዮጵያ ለምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል የምታዋጣውን ሞተራይዝድ ሻለቃ የግዳጅ ዝግጁነት የሚያረጋግጥ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ይታወቃል።

በምሥራቅ አፍሪካ ተጠንቀቅ ኃይል ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ፖል ካሁሪያ ጀማ÷ ልዑኩ በኢትዮጵያ ቆይታው የኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ኃይል ሞተራይዝድ ሻለቃ ጠቅላይ ጦር ሰፈር ተገኝቶ የሻለቃዋን ዝግጁነትና አጠቃላይ ቁመና መመልከቱን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version