የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የምሽት ፈረቃ የኮሪደር ልማት ሰራተኞችን አበረታቱ

By Mikias Ayele

July 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የምሽት ፈረቃ የኮሪደር ልማት ሰራተኞችን አበረታቱ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷አዲስ አበባን እያስዋቡና እያደሱ የሚገኙ ሰራተኞችን በመዘዋወር የሚከናውኗቸውን የሥራ ሂደቶች መመልከታቸውን አንስተዋል፡፡

የሰራተኞችን የሥራ ሂደት ከመገምገም ባለፈ የሌሊት ፈረቃ ሥራ የሚያከናውኑ ሰራተኞችን እራት በመጋበዝ በሥራቸው ይበልጥ እንዲነሳሱ ማበረታታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህ ፕሮጀክት የሚተጉ ሰራተኞችን በመመገብና በማበረታታት ላይ የሚገኙ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችንም አመስግነዋል፡፡