የሀገር ውስጥ ዜና

አለም አቀፍ የሐረር ቀንን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ

By Amele Demsew

July 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 26ኛውን አለም አቀፍ የሐረር ቀን በሐረር ከተማ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦድሪን በድሪ አስታወቁ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ÷ 26ኛውን አለም አቀፍ የሐረር ቀን የሰላም ፣የፍቅርና የአብሮነት ከተማ በሆነችው ሐረር ከሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በታላቅ ድምቀት ለማክበር በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

“ክብረ በዓሉ ህዝባችንን የሚያሰባስብና የሚያስተሳስር ከመሆኑም በላይ አብረን ለመልማትና ለማደግ የሚያስችል እንደሚሆን እምነቴ የፀና ነው” ሲሉም ነው የገለጹት።