አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ የሚገኘውን የአኮቦ ኢትኖ የማዕድን ኩባንያ ጎበኙ፡፡
በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ኡሞድ ኡጁሉ፣ የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር)፣ ሚኒስትር ዴዔታዎች እና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅትም የአኙዋሃ ዞን የሥራ ኃላፊዎች ስለኩባንያው አጠቃላይ ሂደት ገለጻ ያደረጉ ሲሆን÷ ኩባንያው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምርም ተጠቅሷል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላም የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር መከናወኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡