የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራ ልዑክ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የልማት ሥራዎችን እየጎበኘ ነው

By Melaku Gedif

July 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የልማት ሥራዎችን እየጎበኘ ነው።

ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ÷ በዞኑ ከጸጥታ ሥራው ጎን ለጎን እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም ነው ያመላከቱት።

ልዑካኑ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ሥራን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን÷ የዞኑን ጤና ጽ/ቤት ሕንጻም መርቀው ከፍተዋል፡፡

በማርታ ጌታቸው