የሀገር ውስጥ ዜና

ምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

By Amele Demsew

July 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ፡፡

የተያዙ አጀንዳዎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ከቀረቡ በኋላ ጉባኤው የቀረቡትን አጀንዳዎች መርምሮ በሙሉ ድምጽ በማፅደቅ ነው ጉባኤው መካሄድ የጀመረው፡፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትን ጨምሮ ለጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡