አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታኅሳስ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገር ቤት እንዲመጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
የጥሪው ዋና ዓላማም የሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የሀገራቸውን ባህል፣ ታሪክና እሴቶች በአግባቡ እንዲገነዘቡ ለማድረግ ነው።
በዚህም መሰረት ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች የገቡ ሀገራቸውን የጎበኙ ሲሆን÷ የሶስተኛው ዙር ጎብኝዎችም ለተመሳሳይ ዓላማ ወደ ሀገር ቤት መግባት ጀምረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የሁለተኛ ትውልድ ኢትጵያዊያኑ በቆይታቸው በተለያዩ አካባቢዎች የልማት ሥራዎችንና የቱሪዝም መስኅቦችን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል፡፡