አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ወልቂጤ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቀን 9 ሰዓት ላይ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።
በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻሸመኔ ከተማን 2 ለ 0 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች አዲስ ግደይ እና ሱሌማን ሃሚድ ከመረብ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሻሸመኔ ከተማ ከኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ መውረዱ ተረጋግጧል።
በተመሳሳይ ወልቂጤ ከተማ ሃምበሪቾን 2 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ግቦቹን ጋዲሳ መብራቴ እና መድን ተክሉ አስቆጥረዋል።