Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮርፖሬሽኑ ለገበያ ካቀረባቸው ምርቶች 5 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ባለፉት 11 ወራት ከኢንዱስትሪ ኬሚካል ግብዓት ምርቶች 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሁንዴሳ ደሳለኝ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ ኮርፖሬሽኑ በፋብሪካዎቹ የሚያመርታቸውን የኬሚካል ምርቶች ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ያቀርባል።

በተለይም በማዳበሪያ ግብዓት፣ በጎማ ዛፍ ውጤቶች፣ በሲሚንቶ እና መሰል የኬሚካል ምርቶች ምርታማነቱን እና ትርፋማነቱን በማሳደግ በኢኮኖሚው ውስጥ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ባለፉት 11 ወራት ለሀገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ ካቀረባቸው የኬሚካል ምርቶች 5 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ነው የገለጹት፡፡

ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ28 ነጥብ 9 በመቶ በመቶ ብልጫ እንዳለው ለኢዜአ ተናግረዋል።

ኮርፖሬሽኑ በጎማ ዛፍ ልማት ረገድ በከፊልም ሆነ በሙሉ ያቀነባበራቸውን ምርቶች ለደንበኞቹ እያቀረበ ሲሆን÷ በዘርፉ አቅሙን ለማሳደግ የማስፋፊያ ፕሮጀክት እየተገበረ እንደሚገኝ አንስተዋል።

Exit mobile version