Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ ጥያቄ ማቅረቧን ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማዘጋጀት ጥያቄ ማቅረቧን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ ጥያቄ ተቀባይነት እንዲያገኝም የናይጄሪያ የቀድሞ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ዳንኤል አሞካቺና ንዋንኩ ካኑ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ተመርጠው ጥረቶች መጀመራቸውን አንስተዋል።

አህጉራዊውን ታላቅ ውድድር ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ከካፍ ፕሬዚዳንት እና ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ጠቅሰዋል።

ከሰሞኑ የቀድሞ የአፍሪካ ገናና ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ የመምጣታቸው አንዱ ምክንያትም በእግር ኳሱ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ማነቃቃት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

በአላዛር ታደለ

Exit mobile version