የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሱዊዝ ዲያግኖሲስ ማዕከልን ጎበኙ

By Amele Demsew

June 30, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሱዊዝ ዲያግኖሲስ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የሚገኘውን የሱዊዝ ዲያግኖሲስ ማዕከል መጎብኘታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ አስታውቀዋል፡፡

የሕክምና ማዕከሉ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች ባሻገር አዲስአበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ራዕይ ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ በጤናው ዘርፍ የሚሳተፉ ሌሎች የግል ባለሃብቶችን በመደገፍ ከሀገር ወጥተው መታከም የማይችሉ ወገኖቻችን የተሻለ ሕክምና እንዲያገኙ እንዲሁም የውጪ ምንዛሬ ማስቀረት ላይ ጥረት ማድረጋችንን እንቀጥላለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡