Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መተግበሪያ ስትራቴጂ እያዘጋጀች ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችላትን ብሔራዊ የንግድ ቀጣና መተግበሪያ ስትራቴጂ እያዘጋጀች መሆኑ ተገለጸ።

ስትራቴጂውን በተመለከተ በአዲስ አበባ በተካሄደው ምክክር ላይ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ገብረመስቀል ጫላ እንደገለፁት÷ ኢትዮጵያ ለአካባቢያዊና አኅጉራዊ ውኅደት ጠንካራ አቋም አላት።

ይህን ተከትሎም ኢትዮጵያ ነፃ የንግድ ቀጣናውን ካጸደቁ ቀዳሚ የአፍሪካ ሀገራት መካከል መሆኗን ገልጸው ለተግባራዊነቱም በትኩረት እየሠራች መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

አሁን ላይ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና በመሳተፍ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችላት ብሔራዊ የንግድ ቀጣና መተግበሪያ ስትራቴጂ እያዘጋጀች ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በየነ ጴጥሮስ (ፕ/ር) በበኩላቸው÷ ተቋሙ ኢትዮጵያ በአኅጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናው የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የምርምር ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Exit mobile version