አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 206 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (ኤ ኤም ኤን) የብዝኃነትና የትውልድ ድምፅ መሆኑን በተግባር አሳይቷል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በአዲስ መልክ እራሱን በማደራጀት ያስጀመረውን አዲስ ቻናል፣ የብራንዲንግ ሥራ እና የታለንት ሾው ይፋ አድርገናል” ብለዋል፡፡
አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የከተማችን ነዋሪዎች ዐይንና ጆሮ በመሆን፣ ለውጥ በማምጣት፣ መረጃን በመስጠት፣ በማስተማር እና በማዝናናት ሂደት ውስጥ የራሱን አወንታዊ ሚና እየተወጣ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የብዝኃነትና የትውልድ ድምፅ መሆኑንም በተግባር አሳይቷል ነው ያሉት፡፡