የሀገር ውስጥ ዜና

ተባብረን ከሠራን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እንደምናስረክብ አያጠራጥርም – ጠ/ሚ/ ዐቢይ (ዶ/ር)

By ዮሐንስ ደርበው

June 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተባብረን ከሠራን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እንደምናስረክብ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በደሴ ከተማ እና አካባቢው እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን መጎብኘታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልጸዋል፡፡

ከጉብኝታቸው በኋላም ከደሴ ከተማ ከተውጣጡ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር መወያየታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

“በቆይታችን በሁሉም ቦታ እጅግ አመርቂ የሆኑ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውንም አረጋግጠናል” ብለዋል፡፡

ተባብረን ከሠራን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እንደምናስረክብ ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡