የሀገር ውስጥ ዜና

ነገ በሚካሄደው የጎዳና ላይ ሩጫ ምክንያት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ

By Feven Bishaw

June 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ“መቻል ለ ኢትዮጵያ” የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን ምክንያት በማድረግ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

80ኛውን የመቻል ስፖርት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ነገ በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ሩጫ ይደረጋል፤ ሩጫው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው የጎዳና ላይ ሩጫው የአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልል በመሆኑ በውድድሩ ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-

. ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ . ከካዛንቺስ ወደ ባምቢስ . ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ . ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት . ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ . ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ አንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በሩጫ መስመሮቹ ላይ ከሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑንም ገልጿል።