ስፓርት

“መቻል ለ ኢትዮጵያ” የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ነገ ይካሄዳል

By Feven Bishaw

June 29, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “መቻል ለ ኢትዮጵያ” የተሰኘ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በነገው ዕለት ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

የጎዳ ላይ ሩጫው የመቻል ስፖርት ክለብን 80ኛው ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ነው የሚካሄደው፡፡

መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በሚያደርገው የሩጫ ውድድር በርካቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

በዚህም አትሌቶች፣ የመቻል ደጋፊዎች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ የመከላከያ ሠራዊት ኦንላይን ሚዲያ ቡድን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስታውቋል፡፡

ውድድሩ መቻል ባለፉት 80 ዓመታት ለኢትዮጵያ ያበረከተውን አስተዋጽኦ ለማወደስ እና ቡድኑን ለማበረታታ ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በተጨማሪ መቻል ለ ኢትዮጵያ ክብረ በዓል በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።