የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን መሰጠት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን መሰጠት መጀመሩን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዚህም መሰረት በአፋር ክልል ከጅቡቲ ድንበር በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ የሚገኙ የድንበር አካባቢ ነዋሪዎችን በጠረፍ ንግድ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
በንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና ድህረ ፈቃድ ኢንስፔክሽን መመሪያ ቁጥር 935/2015 መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጠረፍ ነጋዴዎች የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን እየተሰጠ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
በዛሬው እለትም በአፋር ክልል ኤልዳአር፣ አፋምቦ፣ አሳይታ እና ገረኔ ወረዳዎች የሚገኙ የጠረፍ ነጋዴዎች ፈቃድ እንደተሰጣቸው ተነግሯል።
በሶማሌ ክልል ከአይሻ፣ ገብለሎ እና አዲጋላ ወረዳዎች የጠረፍ ንግድ ፈቃድ በኦንላይን ይሰጣል መባሉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የጠረፍ ንግድ እንዲነግዱ ፈቃድ የሚሰጣቸው ነጋዴዎች በማህበረሰቡ ተሳትፎ ለተለዩ እንደሚሆንም ተጠቁሟል።