የሀገር ውስጥ ዜና

የስራ እድልን ለማስፋት የሚያግዝ ሥምምነት ተፈረመ

By Amele Demsew

June 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ግራቪቲ ግሩፕ ከተባለ መቀመጫውን በተባበሩት አረብ ኢምሬት ካደረገው ድርጅት ጋር ለዜጎች የስራና የስልጠና እድል ለማስፋት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

በስምነቱ መሠረት ዜጎች በህትመት ዘርፍ ሠልጥነው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን እንደሚያሥችላቸው ነው የተጠቆመው።

ሚኒስቴሩ የዜጎችን የሥልጠና እና የሥራ ዕድል ከፍ ለማድረግ ያለሙ ሥምምነቶችን በመፈፀም በውጭ ሀገራት የሥራ ሥምሪት ሥኬታማ ውጤት ለማሥመዝገብ መሰል ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

ህጋዊ መሠረት ያላቸው ሥምሪቶች እንዲኖሩ በማድረግ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ ሥለመሆኑም ተጠቁሟል።

በሰሎሞን ይታየው