Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 4ኛ ደረጃ በመያዝ ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና 4ኛ ደረጃ በመያዝ ላጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የልዑካን ቡድን አቀባበል ተደርጎለታል።

በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 5 ወርቅ፣ 4 የብርና 1 የነሐስ ሜዳልያ በማግኘት አጠናቅቃለች።

በካሜሩን ዱዋላ አስተናጋጅነት በተካሔደውና ከ27 ሀገራት በላይ የተውጣጡ 2 ሺህ 500 አትሌቶች ላለፉት 6 ቀናት ሲሳተፉበት የነበረው 23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ተጠናቅቋል።

ኢትዮጵያም በ32 ሴት እና በ36 ወንድ አትሌቶች በ19 የአትሌቲክስ የውድድር አይነቶች በመሳተፍ በ5 የወርቅ፣ በ4 ብር እና በአንድ የነሐስ በድምሩ 10 ሜዳልያዎች በማግኘት 4 ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች።

የልዑካን ቡድኑ አባላት ከካሜሩን አዲስ አበባ ሲገቡ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታዎች አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና ወ/ሮ ነፊሳ አልማኻዲ እንዲሁም ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

Exit mobile version