አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት ክልል አቀፍ የበጀት ቀመርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በመድረኩ የ2017 የበጀት ቀመርን በተመለከተ ከባላድርሻ አካላታ ጋር ውይይት ይደረጋል መባሉን ከክልሉ ርእሰ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡