የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

By Feven Bishaw

June 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚከናወኑ ተግባራት በመሳተፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ።

የኦሮሚያ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በሞጆ ከተማ ተካሂዷል።

በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ በደም ልገሳ እና የተለያዩ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሮችን በማከናወን ነው የተጀመረው።

መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ ማቲዎስ ሰቦቃ÷ ወጣቶች ያላቸውን አቅም፣ እውቀት ተጠቅመው በበጎፈቃድ መርሃ ግብሩ በሚከናወኑ ተግባራት በመሳተፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ ግብሩ የደም ልገሳ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ ችግኝ ተከላ እና ሌሎችም ተግባራት ይከናወናሉ ተብሏል።

በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ8 ሚሊየን በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ወጣቶች ከክልሉ ባሻገር በአጎራባች ክልሎች ጭምር በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች እንደሚሳተፉም ተጠቁሟል።

በሳሙኤል ወርቃየሁ