የሀገር ውስጥ ዜና

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጁ ዓላማ በሕግ የሚመራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር ማስቻል መሆኑ ተመላከተ

By ዮሐንስ ደርበው

June 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ዓላማ ጤናማ፣ ፍትሐዊ እና በሕግ የሚመራ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር ማስቻል መሆኑን የፍትሕ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ÷ ሕጉ አራት ዓላማዎች እንዳሉት አብራርተዋል፡፡

ኢኮኖሚያዊ ወንጀሎች እየተበራከቱ መምጣታቸው፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን የተመለከተ ማዕቀፍ እንዲኖር ማስቻል እና ዓለም አቀፍ ግዴታዎችን ለመወጣት ሲባል ሕጉ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም ነው ያስረዱት፡፡

አዋጁን ካለመረዳት በጥራዝ ነጠቅነት የሚሰጡ አስተያየቶች መኖራቸውን አስታውሰው÷ ሕጉ የኢትዮጵያን ተሞክሮና ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እና የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በማየት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩእና ለይኩን ዓለም