Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ አሻድሊ ሀሰን 70 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር 70 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

መርሐ-ግብሩ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ ክልሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የገለጹት አቶ አሻድሊ÷ የሚተከሉ ችግኞችንና የመትከያ ጉድጓዶችን የማዘጋጀት ሥራ መከናወኑን አረጋግጠዋል፡፡

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር በክልሉ 70 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት መጠናቀቁን እና በአንድ ጀንበርም 15 ሚሊየን ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

እየተተከሉና ለተከላ የተዘጋጁ ችግኞች አብዛኛዎቹ ለምግብነት የሚውሉ አትክልትና ፍራፍሬ መሆናቸውም ጠቁመዋል፡፡

ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ነው ያመላከቱት፡፡

Exit mobile version