Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤንች ሸኮ ዞን ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በቤንች ሸኮ ዞን ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባውን የፔቱ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት መረቁ፡፡

ፕሮጀክቱ በዞኑ ግዲ ቤንች ወረዳ የሚገኙ የጻት እና ዲዙ ቀበሌዎችን በማዋሰን የተገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሁለተኛው የግብርና ልማት ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ የተገነባው ፕሮጀክቱ 84 ሔክታር በማልማት ከ600 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version