የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ ከጅቡቲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Melaku Gedif

June 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብቷል፡፡

አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በጅቡቲ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ የሱፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እና ቁልፍ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመስራት መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያና ጅቡቲ በኢኮኖሚ፣ በንግድ እና በወደብ አገልግሎቶች ላይ ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ወያየታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡