አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛኒያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ116 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በመንግሥት በተደረገ የገንዘብ ድጋፍ በዳሬ ሰላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከታንዛኒያ የኢሚግሬሽን ኮሚሽን ጋር በመተባበር የእስር ገዜያቸውን ያጠናቀቁ 116 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከእስር እንዲፈቱ መደረጉ ተገልጿል፡፡
በዚህም የጉዞ ሰነድ በማዘጋጀት ዛሬ ሁለተኛ ዙር ተመላሾት ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸው ነው የተገለጸው፡፡
ከተመላሾች መካከል አንድ ሴት የምትገኝ ሲሆን ፥ ያለፈውን ሣምንት ጨምሮ ቁጥራቸው 160 የሚደርሱ የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት መመለስ መቻሉን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይ ጊዜያት በታንዛኒያ በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙና የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ዜጎችን የመመለሱ ተግባር እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡