Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በፕሪምየር ሊጉ መቻል ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መቻል ሲዳማ ቡናን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችሏል።

የመቻልን ጎሎች ከነዓን ማርክነህ ሁለት ፣ ምንይሉ ወንድሙ በፍፁም ቅጣት ምት እና አማካኙ በሃይሉ ግርማ ቀሪዎቹን ጎሎች ሲያስቆጥሩ ለሲዳማ ብቸኛውን ጎል ብርሀኑ በቀለ ከመረብ አሳርፏል።

መቻል የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን 57 እና ተጨማሪ 16 ጎሎችን በማድረስ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እኩል በመሆን የሊጉን ዋንጫ እየተፎካከረ ይገኛል።

የ2016 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሊጠናቀቅ ሁለት ጨዋታ ብቻ በቀሩት ውድድር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻል እስከ መጨረሻው 30ኛው ሳምንት ለዋንጫ የሚያደርጉት ፉክክር አጓጊ አድርጎታል።

በቀጣይ መቻል ከአዳማ ከተማ ጋር ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋል።

Exit mobile version