Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

1 ሺህ 93 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 93 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡

ከተመላሽ ዜጎቹ ውስጥ 1 ሺህ 87ቱ ወንዶች ሲሆኑ 6ቱ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ47ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተገልጿል፡፡

Exit mobile version