አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ወጣቶች ለዘላቂ ሠላምና አብሮነት እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ።
“የሰላም ባህልና አመለካከትን የመገንባት እና የመምራት ክኅሎት” በሚል መሪ ሐሳብ ከክፍለ ከተሞች ለተውጡ ወጣች በሰላም ላይ የታኮረ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ ዓለማየሁ እጅጉ÷ የአዲስ አበባ ወጣቶች በሰላም እንዲሁም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የነቃ ተሳትፎ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰው በቀጣይም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ልማትን የሚያደናቅፉ የተሳሳቱ መረጃዎችን በሰከነ መንገድ ማገናዘብ፣ አንድ የሚያደርጉ ሐሳቦች ላይ ማተኮር እንደሚገማም ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የመድረኩ ዓላማ የአዲስ አበባ ወጣቶች ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያጠናክሩ ለማድረግ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፕሬዚዳንት መለሰ አባተ ናቸው፡፡