የሀገር ውስጥ ዜና

ኤረር የመጠጥ ውኃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመረቀ

By ዮሐንስ ደርበው

June 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በ224 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባውን ኤረር የመጠጥ ውኃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት መርቀው ሥራ አስጀመሩ፡፡

አቶ ኦርዲን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ በሐረር ከተማ የውኃ ተደራሽነትን ለማሳደግ ኤረር የመጠጥ ውኃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የፕሮጀክቱ መጠናቀቅ የሐረርን ዕለታዊ የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ከ3 ሺህ 500 ሜትር ኪዩብ ወደ 7 ሺህ ሜትር ኪዩብ እንዳሳደገውም አስረድተዋል፡፡

በእዮናዳብ አንዱዓለም