የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

June 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በተባበሩት መንግስታት የህፃናት አድን ድርጅት(ዩኒሴፍ) የኢትዮጵያ ተወካይ በሆኑት አቡበከር ካምቦ(ዶ/ር) ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱን አስመልክቶ አቶ ሽመልስ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው÷”በአቡበከር ካምቦ(ዶ/ር) ከተመራው ልዑክ ጋር በክልላችን የትምህርት ጉዳዮች ላይ ባደረግነው ውይይት፣ ድርጅቱ መንግስታችን ለትምህርት ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት በበጎ መረዳቱንና ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮን ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጦልናል” ብለዋል።

“እኛም በበኩላችን ትምህርትን በሚመለከቱ የትኞቹም ጉዳዮች ተቀራርበን በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆናችንን በድጋሚ አረጋግጠንላቸዋል “ሲሉም ገልፀዋል።